የቅሬታ አቀራረብና አፈታት ሥርዓት
- ቅሬታ ያጋጠመው ተገልጋይ ቅሬታውን በቀጥታ አገልግሎት ለሰጠው ፈፃሚ አካል በቃል፣ በጹሁፍ፣ በስልክ፣ በፋክስና በኢሜል ማቅረብ ይችላል፣
- ቅሬታው የቀረበበት ፈፃሚም የቀረበለትን ቅሬታ አጣርቶ ለአቅራቢው ተገቢውን ምላሽ መስጠት አለበት፣
- በተሰጠው የቅሬታ ምላሽ ያልረካ ተገልጋይ ቀጥሎ ላለው ኃላፊ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል፣
- በዚህ ሁኔታ የቀረበለት የሥራ መሪ /ኃላፊ፣ ቅሬታውን አጣርቶ ምላሽ መስጠት አለበት፣
- ይህም ሆኖ በቂ ምላሽ አላገኘሁም የሚል የአገልግሎታችን ተጠቃሚ በተቋሙ ላለው ቅሬታና አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታውን ያቀርባል፣
- ያም ሆኖ በቂ ምላሽ አላገኘሁም ካለ ለድርጅቱ የበላይ ኃላፊ ማቅረብ ይችላል፣ ኃላፊውም ችግሩን አጣርቶ ተገቢውን ምላሽ መስጠት አለበት፣
- እነዚህን ደረጃዎች ተከትሎ ቅሬታን በማቅረብ እና በተሰጠው የቅሬታ ምላሽ ያልረካ ተገልጋይ እንደ አግባቡ፡-
- ለፌደራል ለሕዝብ እንባ ጠባቢ ተቋም፣
- ለፌደራል የሥነ- ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣
- ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣
- ለመገናኛ ብዙሀን፣
- ለሌላ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎች፣ ተገልጋዮች፣ ቅሬታቸውን ለማቅረብ ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች!-
- ቅሬታ የቀረበበት ዋና ጉዳይ፣
- መንስኤ የሆነውን ድርጊት የተፈፀመበትን ቀንና ቦታ፣
- ጉዳዩ የሚመለከተው የአገልግሎት ክፍልና አገልግሎት ሰጪው ሠራተኛ /ቢቻል ማንነት/፣
- ደጋፊ ማስረጃዎች /ካሉ/
- የባለጉዳዩ ሙሉ ስምና አድራሻ