የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

Full 1
እንኳን ወደ አዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት መጡ
Full 1
Full 2
እንኳን ወደ አዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት መጡ
Full 2
previous arrow
next arrow

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ኀዳር 12 ቀን 1949 ዓ.ም በአዋጅ የተቋቋመ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ሲሆን በተሰጠው ስልጣን መሠረት ጤናማነቱ በእንስሳት ሃኪም የተረጋገጠ የእርድ አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪ ኀብረተሰብ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለኀብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የተለያዩ የአሰራር ዘዴዎችን እየተጠቀመ በርካታ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው፡፡

ሆኖም ለኀብረተሰቡ በጥራትና በብቃት በመስራት የተሟላ እርካታ ከማስፈን አንፃር የድርጅቱ ሥራ በየወቅቱ የሚቀያየር በመሆኑ በርካታ ያልተወጣቸው ችግሮችና አጥረቶች እንዳሉ ከሚሰጠን ጥቆማና አስተያየት መረዳት ተችሏል፡፡

ስለሆነም የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተሰጠውን ስልጣንና የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችለው የተለያዩ የአሠራር ዘዴዎችን ነድፎ የተገልጋዩን ኀብረተሰብ ፍላጐትና ስሜት በጠበቀ መልኩ ደንበኞችን የማርካት ሥራ ለመስራት እያንዳንዱ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚፈጀውን የጊዜ መጠን አውቆ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ስራ ለመስራት የአገልግሎት አይነቱን መለየትና ደንበኞችም ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታ አውቀው በቅድሚያ በማሟላት ተገቢውንና የተሻለ አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ይህ የዜጐች የስምምነት ሠነድ  የድርጅቱን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች አካቶ በሚከተለው መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት

የከተማችን ህብረተሰብ ከምንም በላይ ለጤናው ቅድሚያ በመሥጠት ተመርምሮ ጤናማነቱ የተረጋገጠ ሥጋ ብቻ በመጠቀም ከሁለት መቶ በላይ ከሆኑ አደገኛ ተላላፊ በሽታዎች እራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ እያስገነዘብን፤ ለህብረተሰቡ ጤና ግድ የማይላቸውንና በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚሞክሩ ህገ-ወጥ የሥጋ ነጋዴዎች ሲያጋጥሙት ለህግ አስከባሪ፤ ለጤና ቢሮ፤ ለአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ እንዲሁም ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጥቆማ እንዲያደርግ እያሳሰብን፤ ሀገራችን የነደፈችውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሳካት መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ እንድትሰለፍ መላው ህብረተሰብ ድርሻውን እንዲወጣ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡ የከተማችን ህብረተሰብ ከምንም በላይ ለጤናው ቅድሚያ በመሥጠት ተመርምሮ ጤናማነቱ የተረጋገጠ ሥጋ ብቻ በመጠቀም ከሁለት መቶ በላይ ከሆኑ አደገኛ ተላላፊ በሽታዎች እራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ እያስገነዘብን፤ ለህብረተሰቡ ጤና ግድ የማይላቸውንና በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚሞክሩ ህገ-ወጥ የሥጋ ነጋዴዎች ሲያጋጥሙት ለህግ አስከባሪ፤ ለጤና ቢሮ፤ ለአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ እንዲሁም ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጥቆማ እንዲያደርግ እያሳሰብን፤ ሀገራችን የነደፈችውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሳካት መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ እንድትሰለፍ መላው ህብረተሰብ ድርሻውን እንዲወጣ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

አዲስ አበባ ,ኢትዩጵያ

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት