የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

የዜጐች የስምምነት ሠነድ ዓላማ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለከተማው ነዋሪ ኀብረተሰብ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በመለየት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ተግባራዊ በማድረግ የግልፀኝነቱንና የተጠያቂነቱን ሥርዓት በመዘርጋት ከደንበኞች ጋር የጋራ የሆነ ስምምነት ለመፍጠር ያመች ዘንድ የዜጐች የስምምነት ሠነድ(Citizen Charter)ማዘጋጀት አስፈጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ራዕይ

ደህንነቱ በእንስሣት መርማሪ ባለሙያ የተረጋገጠ የሃገር ውስጥና ኤክስፖርት እርድ አገልግሎት መስጠትና ስጋና የሥጋ ውጤቶችን በማቅረብ  ተወዳዳሪ ሆኖ የደንበኞችንና የኀብረተሰቡን ፍላጐት የሚያረካ ዘመናዊ ቄራ ማድረግ ነው፡፡
ተልዕኮ

· ንጽህናውን:-የጠበቀና ተመርምሮ ጤናማነቱ የተረጋገጠ የእንስሳት አርድ አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ኀብረተሰብ በቅልጥፍናና በታማኝነት መስጠት፣

·     ደህንነቱ:- የተረጋገጠና ደረጃውን የጠበቀ ሥጋ ለተቋሞች፣ ለሆቴሎች … ወዘተ በተወዳዳሪ ዋጋ ማቅረብ፣

·  ከተረፈ ምርት :- የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸውን ምርቶች በጥራት በማምረት መሸጥ፣

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ኀዳር 12 ቀን 1949 ዓ.ም በአዋጅ የተቋቋመ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ሲሆን በተሰጠው ስልጣን መሠረት ጤናማነቱ በእንስሳት ሃኪም የተረጋገጠ የእርድ አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪ ኀብረተሰብ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለኀብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የተለያዩ የአሰራር ዘዴዎችን እየተጠቀመ በርካታ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው፡፡

ሆኖም ለኀብረተሰቡ በጥራትና በብቃት በመስራት የተሟላ እርካታ ከማስፈን አንፃር የድርጅቱ ሥራ በየወቅቱ የሚቀያየር በመሆኑ በርካታ ያልተወጣቸው ችግሮችና አጥረቶች እንዳሉ ከሚሰጠን ጥቆማና አስተያየት መረዳት ተችሏል፡፡

ስለሆነም የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተሰጠውን ስልጣንና የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችሉ የተለያዩ የአሠራር ዘዴዎችን ነድፎ የተገልጋዩን ኀብረተሰብ ፍላጐትና ስሜት በጠበቀ መልኩ ደንበኞችን የማርካት ሥራ ለመስራት እያንዳንዱ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚፈጀውን የጊዜ መጠን አውቆ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ስራ ለመስራት የአገልግሎት አይነቱን መለየትና ደንበኞችም ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታ አውቀው በቅድሚያ በማሟላት ተገቢውንና የተሻለ አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ይህ የዜጐች የስምምነት ሠነድ  የድርጅቱን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች አካቶ በሚከተለው መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት