የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት

የከተማችን ህብረተሰብ ከምንም በላይ ለጤናው ቅድሚያ በመሥጠት ተመርምሮ ጤናማነቱ የተረጋገጠ ሥጋ ብቻ በመጠቀም ከሁለት መቶ በላይ ከሆኑ አደገኛ ተላላፊ በሽታዎች እራሱንና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ እያስገነዘብን፤ ለህብረተሰቡ ጤና ግድ የማይላቸውንና በአቋራጭ ለመበልፀግ የሚሞክሩ ህገ-ወጥ የሥጋ ነጋዴዎች ሲያጋጥሙት ለህግ አስከባሪ፤ ለጤና ቢሮ፤ ለአዲስ አበባ ከተማ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ እንዲሁም ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጥቆማ እንዲያደርግ እያሳሰብን፤ ሀገራችን የነደፈችውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማሳካት መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገሮች ተርታ እንድትሰለፍ መላው ህብረተሰብ ድርሻውን እንዲወጣ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

የድርጅቱ አገልግሎት ምርቶች

  • ጤንነቱ በሐኪሞች ተመርምሮ የተጋገጠ የእርድ አገልግሎት መስጠት
  • ሙሉ የበግ ሥጋ ሽያጭ
  • ለሳሙና መስሪያ በግብዓት የሚያገለግል የተነጠረ ሞራ ሽያጭ
  • የዶ መኖ ማዘጋጃ የሚውል የሥጋና አጥንት መኖ
  • የውሻ መኖ
  • የሾርባ አጥንት እና ሌሎች

የውሻ መኖ

የሾርባ አጥንት

ለተፈጥሮ ማዳበሪያ ለማዘጋጀት የሚውል አጥንት

የተነጠረ ሞራ

ቀንድ

የባለድርሻ አካላት ጋር የሚኖረው መስተጋብር

ቁልፍ ተገልጋይና ባለድርሻ አካላት

በየዕለቱ በሚኖረው ሂደት ውስጥ ለእርድ የሚሆኑ እንስሳትን ወደ ድርጅቱ በማምጣት ጤናማነቱ የተረጋገጠ የእንስሳት ስጋ ለተጠቀሚዎቻቸው ለማቅረብ እርድ እንዲከናወንላቸው ያደርጋሉ

በተለያየ ምክንያት ለተለያዩ ዝግጅቶች የእርድ አገልግሎት የሚፈልጉ ደንበኞች አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ

የስጋና አጥንት፣ ሸሆና እንዲሁም ከተረፈ ምርት የሚገኙ ምርቶችን ለሌሎች ምርትበግብዓትነት ጥቅም ላይ ያውላሉ

በእርድ ወቅት የሚሰበሰቡ የእንስሳት ቆዳና ሌጦዎችን ለቆዳ ምርት ውጤቶች እንደግብዓት ይጠቀማሉ

ታርደው ለደንበኞች ለሽያጭ የሚቀርቡ በጎችን ያቀርባሉ

በድርጅቱ ጤናማነቱ ተመርምሮ ለገበያ የቀረበ የበግ ስጋን በመግዛት ይጠቀማሉ

ከድርጅታችን የእርድ አገልግሎት በማግኘት ለደንበኞቻቸው ደረጃውን የጠበቀ የስጋ አቅርቦት ያከናውናሉ

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት