የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

ዜናዎች

የቴክኒክና ጥገና የሥራሂደት እና የግዥና ንብረት አሰተዳደር  የስራ ሂደቶች የካይዘን ትግበራ እያከናወኑ እንደሚገኙና እስከአሁን ውጤታማ ስራ ማከናወናቸውን አያይዘው ገልፀዋል፡፡

በቴክኒክና ጥገና የሥራ ሂደት በሁሉም የስራ ክፍሎች ውጤታማ የሆነ የካይዘን አሰራር እየተተገበረ እንደሚገኝና በተለይ የቢላ ቤት የስራ  ክፍል ከዚህ በፊት የነበረ የሃብት ብክነት ሙሉ በሙሉ በማስቀረት 100% የካይዘን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ በክፍሉ የሚገኙ  ሠራተኞች ሁለት ብቻ ሆነዉ ነገር ግን ጠንክረው ስለሰሩ አውንታዊ ለዉጥ አምጥተዋል ብለዋል፡፡

አያይዘውም በቴክኒክና ጥገና የሰራ ሃደት ለአሰራር ምቹ ለማድረግ የተለያዩ ስራ እያከናወኑ እንደሚገኙ ከዚህ መካከል የሠራተኞች የልብስ መቀየሪያና ሳጥን ተሰርቶ ማለቁንና የፋይል አደረጃጀት ጥሩ ምሳሌ መሆኑን አያይዘው ገልፀዋል፡፡ በግዥና ንብረት አስተዳደርም የስራ ሂደት በተመሳሳይ ውጤታማ ስራ መሰራቱና ከ30-40 ዓመት ምንም ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ ዕቃዎችን ተለይተው ድርጅቱን በሚጠቅም ሁኔታ እንዲወገዱ መደረጉን የካይዘን ቡድኑ አስተባባሪ በተጨማሪነት ገልፀዋል፡፡

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት