የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

ዜናዎች

በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት 32ኛው የኤችአይቪ ኤድስ ቀን ተከበረ!!

በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት 32ኛው የኤች አይ ቪ ቀን በድምቀት ተከበረ፡፡ በበዓሉ ላይ ተገኝተው የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤች አይ ቪ ኤድስ መቆጣጠሪያና መከላከያ ጽ/ቤት የኤች አይ ቪ ኤድስ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ፈለቀች አንዳርጌ እንደተናገሩት የቫይረሱ ስርጭት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መሆኑንና በተለይ በከተማችን አዲስ አበባ ከጋምቤላ ክልል ቀጥሎ በከፍተኛ ሁኔታ ቫይረሱ እየተስፋፋ መሆኑን  ገልፀዋል፡፡

በከተማችን የቫይረሱ ስርጭት 3.4.% መድረሱን በመግለፅ 105,851 አዲስ አበባ ውስጥ ከቫይረሱ ጋር እንደሚኖሩ ገልፀዋል፡፡ የዚሀ መንስኤ ደግሞ ህብረተሰቡ የተሟላ ገንዛቤ ባለመያዙ መሆኑንና በዚህ መሠረት የተሟላ የኤችአይቪ ኤድስ እውቀት ያላቸው ሴቶች 44.1.%’ ወንዶች 51.5.%’ ብቻ መሆናቸውን አያይዘው ገልፀዋል፡፡

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት