የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

በአዲስ አበባ ቄራዎች የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የድርጅቱ የኪኒሊክ ሓላፊ አቶ ማቲዎስ ግርማ አስታወቁ፡፡

ሃላፊዉ አያይዘዉ እንደገጹት  በአለማችን እንዲሁም በአገራችን ከፍተኛ ስጋት ደቅኖ የሚገኘዉን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ከፍተኛ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ በመግለጽ በዚህም መሰረት በድርጅታችን ዘጠኝ አባላት ያሉት ዓብይ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መገባቱንና በሰራተኞች መግቢያና መዉጫ በሮች ላይ የእጅ መታጠቢያ በማዘጋጀት እንዲሁም የሰራተኞች ሰርቢስ በኬሚካል በማጽዳት 

 

በዉስጥ ሚዲያም በኪኒሊኩ  ባለሙያዎች የቫይረሱን  መተላለፊያ መንገዶችና እንዴት መከላከል እንደሚቻል የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ጥንቃቄ እንዲደረግ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉንና በቀጣይም አብይ ኮሚቴዉ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመሆን መከናወን የሚገባቸዉን ተግባራት እየለየ እንደሚያሳዉቅ ገልጸዉ ሁሉም የድርጅቱ ሰራተኞች የአካባቢያቸዉንና የግል ንጽህናቸዉን በመጠበቅ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከመሆን እራሳቸዉን እንዲጠብቁ መክረዋል፡፡  

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት