የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የሚገነባው አዲሱ ቄራ ፕሮጀክት አካባቢ ከሚኖሩ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ

በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የሚገነባው አዲሱ ቄራ ፕሮጀክት አካባቢ ከሚኖሩ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

በአዲሱ ቄራ ፕሮጀክት በሚገነባበት ቦታ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪች ጋር የውይይትና ምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

 

በውይይት ላይ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ቆንጂት ደበላ እንደገለፁት መንግስት የልማት ስራዎች ሲሰራ የከተማይቱ ነዋሪዎች እንደማይጐዳና የመንግስት ልማት የህዝብ ስለሆነ ከነዋሪዎች ጋር በመመካከር የሚሰሩ ልማት እንጂ ተለያይተን የምንሰራው ልማት እንደሌለና እንደማይገባም አያይዘው ገልፀዋል፡፡ በዚህ መሰረት ለነዋሪዎቹ ሁለት አማራጭ አስቀምጠዋል፡፡ እነሱም

1ኛ በዝቅተኛ ዋጋ የቤት ባለቤት የማድረግ አማራጭ ሲሆን፣

2ኛ ደግሞ ተገቢነትያላቸው ነዋሪዎች ደግሞ በሰነድ አልባ አሰራር መሰረት እንደሚስተናገዱ ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 

ተሳታፊዎች በበኩላቸው መንግስት ይዞት ያለው ፕሮግራምና ዕቅድ የሚደግፍ ነው፡፡ ግን ቶሎ ብሎ ወደ ተግባራዊነቱ ቢገባና ልማቱን ቶሎ ቢጀምር ጥሩ ነው የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ በውይይቱ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር  አቶ ሰይድ እንድሪስን ጨምሮ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ተገኝተው ለተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት