የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በላከልን መልዕክት ይህን ወቅት በመደጋገፍ ለማለፍ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ አሳውቆናል። በሌላ በኩል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልጾልናል

ድጋፍ እና እገዛን በሚመለከት ፦

– ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከላከል እና መቆጣጠርን በተመለከት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።

– ድርጅቱ በሚገኝባቸው ወረዳዎች እና አጎራባች ወረዳዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ለ400 ሰዎች እገዛ እና ድጋፍ አድርጋል።

– ተቋሙ ለሚያሳድጋቸው 15 ወላጅ አልባ ህፃናት በየወሩ የሚያደርገው ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ የዘይትና የዱቄት ድጋፍ አድርጋል።

የእርድ እና የስጋ ስርጭት አገልግሎትን በሚመለከት ፦

– የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው። ቀዳሚ የነበረው ሰራተኞችን ማሰልጠን፣ ግንዛቤ መስጠት፣ በተለይም ሚኒ ሚዲያውን በመጠቀም ተሰርቷል።

– ድርጅቱ የሙቀት መለኪያ አስገብቶ ሰራተኞች ሲገቡ ሙቀታቸው እንዲለካ፣ የእጅ ጋንት፣ ሳኒታይዘር እና ሌሎች የንፅህና መጠበቂየዎች እንዲሰጥ ተደርጓል።

– ተሽከርካሪዎች ከከተማ ሲመጡ የኬሚካል ርጭት እየተደረገ ይገኛል። ኬሚካል ርጭቱ ሊያገኛቸው የማይችሉ የመኪና ክፍል (በተለይም የጎማ ክፍል) ‘ማለፊያ ቦታ’ ተሰርቶ መኪናዎች ጎማቸው በኬሚካል እንዲፀዳ እየተደረገ ነው።

– እንስሳት ሲገቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ተደርጎ እየተሰራ ነው፣ የእርድ ክፍሎች ሴራሚክ ተደርገዋል፤ ክፍሎቹ ፅዳታቸውን በየጊዜው ይጠበቃል።

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት