የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በከተማ አስተዳደሩ የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ዘርፍ ስር የሚገኝ ተቋም እንደመሆኑ መጠን የድርጅቱን ምርታማነት ለማሳደግ እና በተቋሙ የሚስተዋለውን የተደራሽነት ችግር፣ የደንበኞች የአገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ አለመሆን፣ የሠራተኛው ተነሳሽነት ማነስ፣ የአካባቢ ብክለት መጨመር አሳሳቢና ፈጣን ምላሽ የሚፈልግ በመሆኑ በ2013 ዓ.ም በተቋሙ ስራ አመራር ቦርድ እና በማኔጅመንቱ ውሳኔ መሠረት የካይዘን ትግበራ ወደ ስራ እንዲገባ መደረጉ ይታወቃል፡፡

በዚህም ከፍተኛ የአገልግሎት አሰጣጥ ማነቆዎችን በመፍታት፤ የድርጅቱ የእርድ አገልግሎት እና የተረፈ ምርት ምርታማነትን መጨመር እንዲሁም በዋነኝነት የድርጅቱ አሳሳቢ ችግር የነበረው የአካባቢ ብክለት እና መጥፎ ሽታ እንዲጠፋ በማድረግ ክፍተኛ ስራ ተሰርቷል ሲሉ የድርጅቱ አማካሪ አቶ ከበደ ፀጋዪ ተናግረዋል፡፡

በተቋሙ የካይዘን ትግበራ በመከናወኑ የሰራተኞች የስራ ቦታ ደህንነት መጠበቅ መቻሉ እንዲሁም ንጹህ እና ምቹ የስራ ቦታ በመፈጠሩ ሠራተኞች ስራቸውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲያከናውኑ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የአገልግሎት ጥራትን ለማሳደግ በካይዘን ትግበራ የሚፈለጉ ዶክመንቶችንና መሳሪያዎችን ከ30 ሰከንድ ባነሰ ጊዜ ማግኘት መቻል እንዲሁም የስራ ቦታን በአግባቡ በማደራጀትና የማምረቻ መሳሪያዎችን እንክብካቤ በማድረግ ምርትንና ምርታማነትን በመጨመር እረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከመኖሩም በላይ የካይዘን ትግበራን በማከናወን ድርጅቱን ካላስፈላጊ ወጪ በማዳን ጥቅም ላይ ሊውሉ ያልቻሉ ግብአቶችን ወደ ገንዘብ እንዲለወጡ በማድረግ ተቋሙ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ መደረጉ ድርጅቱ ካይዘንን በአግባቡ በመተግበሩ የተገኘ ውጤት ነው ሲሉ አማካሪው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት