በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት 15ኛዉ የባንዲራ ቀን ‹‹ሰንደቅ አላማችን የብዝሀነታችን መገለጫ፤የሉአላዊነታችን ምሰሶ›› በሚል መሪ ቃል ተክብሯል፡፡በሥነ-ሥርዓቱ ላይም የድርጅቱ ሰራተኞችና የስራ ሃላፊዎች በመገኘት ባንዲራ በመስቀል እና የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር በጋራ በመዘመር አክብረዉት ዉለዋል፡፡