የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

ጳጉሜ 3፤ቀን 2014 ዓ.ም

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከ 6 ሺ እስከ 7 ሺ የሚሆን የእንስሳት ዕርድ ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰይድ እንድሪስ ገልፀዋል።

ለኅብረተሰቡ ንፅህናውን የጠበቀ የእርድ አገልግሎት በፍጥነት እና በቅልጥፍና ለማቅረብ የእርድ መሳሪያዎች እንዲሁም የስጋ መጓጓዣ መኪናዎች ዝግጁ መሆናቸውን ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

በዕለቱ የሰው ኃይል እጥረት እንዳያጋጥምም ድርጅቱ ከ 200 በላይ ጊዜያዊ ሰራተኞች መቅጠሩን ሀላፊው ጨምረው ገልፀዋል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበርና የኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ነጋዴዎች ማኅበርም ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ከ9 እስከ 10 ሺህ የሚጠጉ የእርድ እንስሳቶች ወደ ከተማዋ የግብይት ስፍራዎች እንዲገቡ መደረጋቸውን የኢትዮጵያ የቁም እንስሳት ነጋዴዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መአዛ ቀለምወርቅ አስታውቀዋል ፡፡

በከተማዋ የሚገኙ ልኳንዳ ቤቶች በተመመጣጣኝ ዋጋ በቂ የስጋ አቅርቦት እንደሚኖር የገለፁት የአዲስ አበባ ልኳንዳ ነጋዴዎች ማኅበር ስራ አስኪያድ አቶ አየለ ሳህሌ ህብረተሰቡ ከበዓሉ እለት ጀምሮ አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችል ተናግረዋል።

በቤትና በተለያዩ አካባቢዎች የሚከናወኑ እርዶች ከእንስሳት ወደ ሰው ለሚተላለፉ በሽታዎች ተጋላጭ ስለሚያደርጉ፥ ህብረተሰቡ በቄራ ብቻ የታረደ ስጋ በመመገብ የራሱን እና የቤተሰብን ጤና እንዲጠብቅ በማለት ጥሪ ቀርቧል።

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት