የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise


መስከረም 2፤ቀን 2015 ዓ.ም
ድርጅቱ በበዓላት ወቅት በቁጥር በዛ ያሉ እንስሳቶችን በማረድ ንፅህናውን የጠበቀ እና የተመረመረ ስጋ ለህብረተሰቡ እንደሚያቀርብ ይታወቃል፡፡
ስለሆነም በሁለቱ ተከታታይ ቀናት ማለትም ጳጉሜ 4 እና 5 በድምሩ 3798 ትላልቅ እንስሳት ፣ 4,432 ትናንሽ እንስሳት/ በግ እና ፍየል/ በጥቅሉ 8,230 የእንስሳት እርድ መከናወኑን አስታዉቋል፡፡

የድርጅቱ የስጋ ስርጭትና የእርድ አገልግሎት የስራ ሂደት ለአገልግሎቱ ሰራተኞችና ድጋፍ ላደረጉ አካላት ባቀረበዉ ምስጋና ላይ እንደተገለጸዉ በሁለቱ ቀናት በነበረዉ የእርድ አገልግሎት የተሳካ ስራ መሰራቱን ጠቅሶ የምስጋናና የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክቱን አስተላልፏል ፡፡አያይዞም በአዲሱ ዓመት ተቋሙ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረዉ የደንበኞችን እርካታ ለመጨመር የተሻለና ጥራት ያለዉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በተለየ ሁኔታ እንደሚሰራ በመጠቆም በዓሉ የስኬት የአንድነት የደስታ እንዲሆን ተመኝቷል ሲል የዘገበዉ የድርጅቱ የኢንፎርሜሽንና ህዝብ ግንኙነት አገልግሎት ነዉ፡፡

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት