የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አመራርና ሰራተኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ሙስናን በጋራ እንከላከል በሚል መሪ ቃል የጸረ ሙስና ቀንን አክብረዋል ፡፡
በመረሀ ግብሩ ወቅት የተቋሙ የጸረ ሙስና ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ አባተ በሰነድ የተደገፈ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን እንደተቋምም ሆነ እንደ ሀገር ሙስናን መታገል የእያዳንዱ ሰዉ ሀላፊነት እንደሆነና የችግሩ አሳሳቢነትም የተቋምንም ሆነ የሀገርን ጥቅም በከፍተኛ ደረጃ እየጎዳ የሚገኝበት ወቅት ላይ በመሆናችን ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ ሰጥተን በአንድ አይነት አስተሳሰብና በተስተካከለ ስነ ምግባር ችግሩን የማክሰም የጋራ ሃላፊነት እና የማያቋርጥ ተግባራዊ ስራ እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል