የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት 8868 የስልክ መስመር ከዛሬ ጀምሮ በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለፀ!

በመንገድ ግንባታ ምክኒያት ተቋርጦ የነበረው የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት 8868 የስልክ መስመር ከዛሬ ጀምሮ በይፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለፀ!

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የስልክ መስመር የሆነው 8868 ለእረጅም ዓመታት ለድርጅቱ ደንበኞች አገልግሎት ሲሰጥ የነበረ የስልክ ጥሪ መቀበያ መስመር እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ይህ የስልክ መስመር ከፑሽኪን አደባባይ እስከ ጎተራ ቄራ የመንገድ ግንባታ ስራ ምክኒያት ላልተወሰነ ጊዜ አገልግሎት መስጠት አቁሞ የነበረ ቢሆንም የመንገድ ግንባታው መጠናቀቁን ተከትሎ የጥሪ መቀበያ መስመሩ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ሲሉ የድርጅቱ የእንፎረሜሽን እና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ሃላፊ አቶ ጥበበ ጥሩነህ ገልፀዋል፡፡

ይህ የጥሪ መቀበያ መስመር ከደንበኞች የሚመጡ ጥቆማዎችን አንዲሁም የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችን በመቀበልን ተቋሙ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን እና ጠንካራ ጎኖችን ለመለየት እና መፍትሄ ለመስጠት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን ደንበኞችን ከድርጅቱ ጋር የሚያገናኝ አንዱ መንገድ ነው ሲሉ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ውድ ደንበኞቻችን የእናንተ ማንኛውም አይነት ጥቆማ እና አስተያየት ለተቋሙ እድገት እና ብልፅግና አስተዋፅኦ ከፍተኛ ስለሆነ የስልክ ጥሪያችሁን በትህትና ተቀብሎ የሚያስተናገድ በቂ የሰው ሀይል አዘጋጅተን ወደ ስራ የገባን በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጡን በተመለከተ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት 8868 የስልክ መስመር ላይ ደውለው ሀሳብ አስተያታቸውን በመስጠት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ ሲሉ ሃላፊው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት