የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

በድርጅቱ ተሸከርካሪዎች ላይ የጂፒኤስ (GPS) ቴክኖሎጂ ተግባራዊ መደረጉ የተቋሙን የሃብትና የጊዜ ብክነትን ለመቀነስ አስዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ!

ጂፒኤስ (Global Positioning system) በማኛውም ጊዜ እና ቦታ በየትኛውም የአየር ሁኔታ ውስጥ በምድር ላይ ትክክለኛ መገኛን ማሳየት የሚችል ብቸኛ ቴክኖሎጂ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ የመንግስትና የግል ተቋማት በተሽከርካሪዎቻቸው ላይ ጂፒኤስ (GPS) በማስገጠም የዚህ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

ከእነዚህ ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የቴክኖሎጂውን ጠቀሜታ እና አስፈላጊነቱን በማመን ድርጅቱ ሰባ አንድ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎቹ ላይ ጂፒኤስ (GPS) እንዲገጠም በማድረግ ወደ ስራ ገብቷል ሲሉ የድርጅቱ የተሸከርካሪ ስምሪት ሱፐርቫይዘር አቶ አንማው ካሳሁን ገልፀዋል፡፡

ጂፒኤስ (GPS) በዋነኝነት የተሽከርካሪዎችን መነሻ እና መድረሻ ፣ጊዜና ቦታን እንዲሁም የፍጥነት መጠንን በቀላሉ ማሳወቅ የሚችል በመሆኑ የነዳጅ ፍታጆውንም ለመቀነስ አመቺ እድል ፈጥሯል በማለት ለአገልግሎት ሊውል ከነበረው የነዳጅ ፍጆታ በአንድ ወር ውስጥ እሰከ 900 መቶ ሊትር ነዳጅ መቆጠብ የተቻለ ሲሆን ቴክኖሎጂው ከዚህ ቀደም በድርጅቱ የሚስተዋለውን የሃብትና የጊዜ ብክነት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል ማለት ይቻላል ሲሉ የክፍሉ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አሽከርካሪዎች ከተፈቀደላቸው የአቅጣጫ ወሰን እና የፍጥነት መጠን ውጪ በሚያሽከረክሩበት ወቅት በተሸከርካሪዎቹ ላይ የተገጠመው ጂፒኤስ (GPS) ምልክት የሚያሳይ በመሆኑ አሽከርካሪዎች በተፈቀደላቸው የፍጥነት ወሰን ልክ ብቻ እንዲያሽከረክሩ ያስገድዳል በማለት ከተፈቀደው የአቅጣጫ ወሰን ውጪ ሲያሽከረክሩ የተገኙ አሽከርካሪዎች የስነስርዓት እርምጃ እንደተወሰደባቸው በመግለጽ በቀጣይም በሁሉም የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጂፒኤስ (GPS) ለማስገጠም በእቅድ ተይዞ ወደ ስራ ተገብቷል ሲሉ የስምሪት ሃላፊው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት