የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
Addis Ababa Abattoirs Enterprise

ህገወጥ እርድን በመከላከል ረገድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተልእኳቸውንና ሃላፊነታቸውን በተገቢ መወጣት እንዳለባቸው ተመለከተ።
የአዲስ አበባ ስራ አስኪያጅ ፅ / ቤት ባዘጋጀው መድረክ የህገወጥ እርድ መስፋፋት በአዲስ አበባ ከተማ በአካባቢ በክለት፣ በህብረተሰብ ጤናና በከተማው ገቢ አሰባሰብ ላይ እያሳደረ ያለውን አሉታዊ ጫና በማስገንዘብ የሚመለከታቸው ተቋማት ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጋር በቅንጅት ህገወጥነትን ሊከላከሉ እንደሚገባ በአፅንኦት ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ፣ ከአካባቢ ጥበቃና ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፣ እንዲሁም ከምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች ህገወጥ እርድን በመከላከል ረገድ እስካሁን ተቋማት በተናጠል መንቀሳቀሳቸው የሚፈለገውን ውጤት እንዳላመጣ ገልፀው የስራ አስኪያጅ ፅ/ ቤት የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ፎረም ማቋቋሙ ችግሩን በጋራና በዘላቂነት ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አረጋግጠዋል።

ዲዛይን እና የተገነባው በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት