የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ኀዳር 12 ቀን 1949 ዓ.ም በአዋጅ የተቋቋመ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ሲሆን በተሰጠው ስልጣን መሠረት ጤናማነቱ በእንስሳት ሃኪም የተረጋገጠ የእርድ አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪ ኀብረተሰብ በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
ድርጅቱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለኀብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የተለያዩ የአሰራር ዘዴዎችን እየተጠቀመ በርካታ አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገበ ነው፡፡
ሆኖም ለኀብረተሰቡ በጥራትና በብቃት በመስራት የተሟላ እርካታ ከማስፈን አንፃር የድርጅቱ ሥራ በየወቅቱ የሚቀያየር በመሆኑ በርካታ ያልተወጣቸው ችግሮችና አጥረቶች እንዳሉ ከሚሰጠን ጥቆማና አስተያየት መረዳት ተችሏል፡፡
ስለሆነም የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተሰጠውን ስልጣንና የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችለው የተለያዩ የአሠራር ዘዴዎችን ነድፎ የተገልጋዩን ኀብረተሰብ ፍላጐትና ስሜት በጠበቀ መልኩ ደንበኞችን የማርካት ሥራ ለመስራት እያንዳንዱ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚፈጀውን የጊዜ መጠን አውቆ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ስራ ለመስራት የአገልግሎት አይነቱን መለየትና ደንበኞችም ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታ አውቀው በቅድሚያ በማሟላት ተገቢውንና የተሻለ አገልግሎት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ይህ የዜጐች የስምምነት ሠነድ የድርጅቱን ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች አካቶ በሚከተለው መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡